ሀገራችን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ጥቂት ሀገራት ተርታ ከተሰለፈች ሁለት አስርት አመታት ማስቆጠሯ የሚታወቅ ነዉ። ሀገራችን በተከታታይ ባለ ሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት ከማስመዝቧ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ሀገራት፣ የአለም ባንክና የአለማቀፍ የገንዘብ ተቋም IMFን ጨምሮ በአለም አቀፍ ተቋማት አድናቆትና እዉቅናን ማትረፍ የቻለች ሀገር ሆናለች። ይህ አስደናቂ ልማትና እድገት ሊመዘገብ የቻለዉ ኢትዮጵያ የምትመራባቸዉ የልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች የሀገሪቷን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያስገባ፣ አዋጭና ትክክለኛ የልማታዊ መንግስት ፖሊሲ በመከተላችን መሆኑ እሙን ነዉ። ሀገራችን የምትከተላቸዉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ስኬታማነት አንዱ ማሳያ ፈጣን እድገትን በማስመዝገብ ህዝባችን በየደረጃዉ እኩል ተጠቃሚ የሚሆንበት ምቹ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት እየተሰራ ያለዉ ስራ ነዉ። 

የዉጭ ግንኙነትና ሀገራዊ ደህንነት ፖሊሲያችን ሰላም፣ ዴሞክራሲና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት የፖሊሲዎቻችን ሁሉ ምሶሶዎችና የህልዉና ጉዳይ መሆኑን በግልጽ ያስቀመጠ ሰነድ ነዉ። ፖሊሲዉም ሆነ ስትራቴጅዉ በዋነኝነት የሚያጠነጥኑት ህዝቡ በየደረጃዉ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ፈጣን ልማትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን እዉን በማድረግና ለዚሁ የተመቻቸ ሁኔታን በመፍጠር ዙሪያ ነዉ።  መንግስት ዜጎች የሚፈልጉት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም አልፎ አልፎ የሚከሰቱትን የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባርና መገለጫዎች በየጊዜዉ ምንጫቸዉን እየፈተሸ የማስተካከያ እርምት በመዉሰድ ህዝብ የሚፈልገዉን አገልግሎት አርኪ በሆነ መልኩ በመስጠት ረገድ ያለዉን የአቋም ቁርጠኝነት በተደጋጋሚ በተግባርና በመርህ አሳይቷል።

መንግስት እያንዳንዱ የመንግስት መስሪያ ቤት የሚሰጠዉን አገልግሎት ቀልጣፋ እንዲሆንና ዜጎችን ላላስፈላጊ እንግልት እንዳይዳረጉ መረጃዎችን በግልጽ በሚታይ ቦታ በመለጠፍ ወይም በመስሪያ ቤቶቹ ድረ ገጽ ላይ እንዲታወቁ ያበረታታል። ሚሲዮናችንም ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት ኤምባሲዉ የሚሰጣቸዉ አግልግሎቶችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ወቅታዊና ጠቃሚ መረጃዎችን በቀጠር ለሚገኙ ዜጎቻችን ሲያደርስ ቆይቷል። አሁንም እያደረሰ ይገኛል።

በቀጠር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር የክቡር መታሰቢያ ታደሰ መልዕክት

​የአምባሳደር መልእክት

ኤምባሲዉ የተለያዩ መረጃዎችን እና መልዕክቶችን ለህዝባችን ለማድረስ ከሚጠቀምባቸዉ ዘዴዎች መካከል የኤምባሲዉ ደረ-ገጽ፣ ፌስ ቡክ፣ ትዊተርና ዩቱብ ናቸዉ። በመሆኑም በቀጠር የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን ኤምባሲዉ የተከፈተበት ዋነኛዉ አላማ ዜጎቻችንን ለማገልገል እንደመሆኑ የምትፈልጓቸዉን የተለያዩ አገልግሎቶችን ከማግኘት ጀምሮ በምትኖሩበት ሀገር ሙሉ መብታችሁ ተክብሮላችሁ በተሰማራችሁበት የስራ መስክ ዉጤታማ ሆናችሁ ራሳችሁን ቤተሰቦቻችሁን እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ሀገራችሁን ለማገልገል ለምታደርጉት ጥረት ኤምባሲዉ ሁሌም ከጎናችሁ እንደሚቆም በድጋሚ ማረጋገጥ እንወዳለን።  

ኤምባሲችን በቀጠር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን መብታቸዉ ተከብሮላቸዉ በተሰማሩበት የስራ መስክ ሁሉ ዉጤታማ እንዲሆኑ በትጋትና በቁርጠኝነት ይሰራል። በተጨማሪም ከሀገር ቤት የሚተላለፉ መረጃዎችን በማድረስ መብታቸዉንና ግዴታቸዉን አዉቀዉ ማግኘት የሚገባቸዉን አግልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል። 

ይህንን በመረዳት በቀጠር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን በኤምባሲያችን በአካል በመቅረብ የሚፈልጉትን አግልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን ለተጨማሪ መረጃ የሚሲዮናችን የፌስ ቡክ፣ ትዊተርና ዩቱብ ገጾቻችንን እንዲጎበኙ በአክብሮት እንጠይቃለን።  

Comment in the box and send it

Useful link

 News