የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ-ዶሃ 

ለጥንቃቄ

በርካታ ዜጎቻችን ከጋብቻ ውጭ በሚፈጠር እርግዝና በወንጀል በመጠየቅ ላይ ናቸው። በቀጠር ህግ መሰረት ከጋብቻ ውጭ የሚፈጠር እርግዝና እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል።

በዚህ መሰረት ችግሩን ለመከላከል

  • በጋብቻ ለመተሳሰር የምትፈልጉ ጥንዶች በጋራ ለመኖር የጋብቻ ማስረጃ መያዝ እንደሚገባችሁ፣

  • ከጋብቻ ውጭ ከሚደረግ ግንኙነት  በመታቀብ ሊደርስባችሁ ከሚችለው እስራት ራሳችሁን እንድትጠብቁ፣

  • ለወደፊት በጋብቻ ለመተሳሰር የሚትፈልጉ ጥንዶች የተለያዩ የእርግዝና መከላከያዎች በቀጠር በሚገኙ የመድሃኒት መደብሮች የሚገኝ በመሆኑ ይህንኑ በመጠቀም ራሳችሁን ከአላስፈላጊ እስራት እንድትጠብቁ።

 News