የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ-ዶሃ 

በዶሃ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ የቆንስላ አገልግሎት ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች

 

አጠቃላይ ሁኔታ

 • የሥራ ቀናት

o    የቆንስላ አገልግሎት ከእሁድ እስከ ሐሙስ ክፍት ነው፣

o    ከ8፡00AM-2፡00PM አገልግሎት ይሰጣል፣

o    ቆንስላ አገልግሎቱ በኢትዮጵያና ቀጣር የሕዝብ በዓላት ቀን አገልግሎት አይሰጥም፣

 

 ከኤምባሲ መረጃ ለማግኘት፣

Um Guwaifa street No, 804

Area Al katifia No, 66 Al-Dafna,

Doha, Qatar በሚገኘው ኤምባሲያችን በአካል በመገኝት ወይም

በስልክ ቁጥር  (00974) 40207000  እና

በE-mail ethio@ethiopiaembassydoha.org  ወይም Consular@ethiopiaembassydoha.org  መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

ወይም በፋክስ ቁጥር 44719588

 

ፎቶ ግራፍ

 • ለሁሉም አገልግልት የሚቀርቡ ፎቶግራፎች የፓስፖርት መጠን ያላቸው ሆኖ መልኩ ከጀርባ ነጣ ያለ ሁለቱንም ጆሮ የሚያሳይ፣ ከሃይማኖት ምክንያት ውጭ ኮፍያ እና ሌሎች ራስን የሚሽፍኑ ነገሮችን ተደርጎ ያልተነሳ መሆን አለበት፡፡

 • ከፎቶ ጀርባ የባለቤቱን ሙሉ ስም መፃፍ አለበት፣

 • ለፓስፖርትና ለመታወቂያ አገልግሎት የሚውል ፎቶ ከጠቅላላ ቦታ 50 እጅ ፊት መሸፈን አለበት፡፡

የተለያዩ ሰነዶችን የማረጋገጥ አገልግሎት

 • ማንኛውም ለማረጋገጥ የሚመጡ ዶክመንቶች ከቀጣር መንግስት የመነጨ ከሆነ (ለምሳሌ - ያላገቡ መሆነዎትን የሚያረጋግጥ፣ የልደት የምስክር ወረቀት እና የመሳሰሉትን …) መጀመሪያ ቀጣር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶኩመንቱን ተረጋግጦ ወደ ኤምባሲው መምጣት አለበት፡፡

 • ለማረጋገጥ የሚፈልጉት ዶኩመንት ከኢትዮጵያ የመነጨና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ከሆነ በቀጥታ ወደኛ በመላክ/በማምጣት አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ

 

በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ ከኢትዮጵያ ለመጡ የተለያዩ ሰነዶችን ለማረጋገጥ

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

 1. መጀመሪያ ለማረጋገጥ የሚፈለጉ ዶኩመንቶች በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተረጋግጦ መቅረብ አለባቸው፣

 2. የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ በማቅረብ ሲፈፅሙ፣

 3. የአገልግሎት ክፍያ መጠን 54.4 ዶላር 198 ቀጣር ሪያል ነው፣

 4. የሌላ አገር ዜጋ ከሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ የሌላቸው/ አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው የጋብቻ፣ የልደት፣ የትምህርት መረጃ… የአገልግሎት ክፍያ መጠን 86.9 ዶላር  316 ቀጠር ሪያል

ከቀጣር መንግስት ለተሰጡ የተለያዩ ዶክመንቶችን ለማረጋገጥ

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

 1. መጀመሪያ በቀጣር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶክመንቶቹ ተረጋግጦ ወደ ኤምባሲው መምጣት አለበት፡፡

 2. የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ በማቅረብ

 3. የአገልግሎት ክፍያ መጠን 52.00 ዶለር ክፍያ ሲፈፅሙ፣

 4. የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ የሌላቸው/ አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው 78.00 ዶላር ክፍያ ይፈፅሙ፣

VI. ከወንጀል ነፃ መረጃ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

 • 2 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)፣

 • የታደሰ ፓስፖርት ወይም የጋብቻ / የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ወይም ሌሎች በኢትዮጵያ መንግስት የተሰጡና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ፣

 • የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ዋናውን ማቅረብ፣

 • የአገልግሎት ክፍያ $54.4 ዶላር/ 198 ቀጠር ሪያል

   ወደ አገር ቤት ሲልኩ

 • ኦርጅናል የጣት አሻራ ዶክመንት ወደ ፌደራል ፖሊስ ፎሬንሲክ ምርመራ ክፍል በአካል፣ በተወካይ ወይም በፖ.ሣ.ቁ. 80358 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በማለት

 • የጣት አሻራ ዶክመንት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ (ኢትዮጵያ)፣

 • ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣

 • ፓስፖርት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ኮፒ መላክ/ማቅረብ

 • ከፌደራል ፖሊስ የተሰጠ መረጃ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኤምባሲው በማረጋገጥ አገልግሎት ላይ ማዋል፣

 • አገር ቤት አገልግሎቱን በአካል ወይም በተወካይ ማግኘት ይቻላል፡፡

 News