የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ-ዶሃ 

Headline News

May 16, 2017

 

መሰረቱን በዶሃ ያደረገውና በመካከለኛው ምስራቅ ግዙፍ የሪል ስቴት ልማት ዘርፍ የተሰማራው ኤዝዳን ሆልዲንግ ካምፓኒ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስክ ለመሰማራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ትናንት ተፈራረ።

የኩባንያው ለቀ መንበር ዶክተር ካሊድ ቢን ታኒ ቢን አብደላህ አል ታኒ ጨምሮ ሌሎች የኩባንያው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ዛሬ ከኤፌዲሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፣ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድሪባ ኩማ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የልዑካን ዱድን አባላት ጋር  ያደረጉት ውይይት ተከትሎ የተፈረመው ስምምነት ኩባንያው በአዲሰ አበባ ከሶስት መቶ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ በሆነ ወጭመ ሊያሰገነባ ያላቀደውን የባለ አምስት ኮከብ ዘመናዊ ሆቴል ግንባታ ፕሮጀክት ተፈፃሚ ለማድረግ የሚያስችለው ነው

ካምፓኒው በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት በያዘው እቅድ መሰረት ከዚህ ቀደም ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጉ የሚታወስ ነው።

 

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚያደርጉት ድጋፍ በአገራቸው ጉዳይ ላይ ያላቸው ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡበት ልዩ ክስተት ነው። በኳታር የኢፌዲሪ ኤምባሲ

በኳታር የኢፌዲሪ ኤምባሲ በዶሃ ከሚገኘው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ጋር በመሆን የህዳሴው ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 6ኛ ዓመት በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አክብረዋል።

=========================//=============================

በትናንትናው ምሽት በኳታር ዶሃ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ሚሲዮኑና በዶሃ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ያካሄዱት የህዳሴው ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 6ኛ ዓመት በዓል የግድቡን የግንባታ ሂደትና ፋይዳ በሚዘክሩ እና በቦንድ ሽያጭና ገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራሞችን እንዲሁም እውቅና የመስጠት ፕሮግራሞችን በማካተት ተከናውኗል ።

በዝግጅቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በኳታር የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እንዳመለከቱት የግድቡ ግንባታ በአሁኑ ወቅት ግድቡ 58 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት የሚያመነጩ 2 ዩኒቶች በዚህ አመት ስራ የሚጀምሩ ሲሆን በሌላ በኩል 6000 ሜጋ ዋት ያመነጫል ተብሎ የተቀመጠው የግድቡ አቅም በቅርቡ የድዛይን ማሻሻያ ተደርጎለት ወደ 6450 ሜጋ ዋት አድጓል። ይህም ከጥቂት አመታት በኋላ አሁን አገራችን እያመነጨች የምትገኘውን 4260 MW ኤሌክትሪክ ሃይል ወደ 10̣‚700 ሜጋ ዋት ያሳድገዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል።

የግደቡ መገንባት እንደ ስጋት ያዩትን የአባይ ተፋሰስ አገራትን በግድቡ ላይ አዎንታዊ አመለካከት አንዲኖራቸው ለማድረግ በተደረገው መጠነ ሰፊ ዲፕሎማሲያዊ ­ጥረትም  ሁሉም የተፋፈሱ አገራት የግድቡን ጠቀሜታ እንዲረዱና እንዲደግፉ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፣ ይህንኑ ተከትሎም አብዛኞቹ ከአገራችን የኤሌክትሪክ ሀይል ለመግዛት ስምምነቶችን እስክመፈራረም መድረሳቸውን አምባሳደር ምስጋኑ ተናግረዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአገር ቤት እንደተስተዋለው ሁሉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑም የግድቡን ግንባታ ዳር ለማድረስ ቃል በገቡት መሰረት በሚያስገርም ሁኔታ የአመለካከት ልዩነት ሳይገድባቸው ለግድቡ ግንባታ ቦንድ በመግዛትና ስጦታ በማበርከት እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች ገቢ በማሰባሰብ ዘመቻዎች ላይ ሲረባረቡ መቆየታቸውን አውስተዋል።

በእስካሁኑ አጠቃላይ የገቢ ማሰባሰበ ስራው 10 ቢለየን ብር ገደማ ለግድቡ ግንባታ መሰብሰበቡንና ከዚህም ውስጥ በኳታር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ያደረጉት የቦንድ ግዥ እና ገቢ ማሰባሰብ ስራ ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ መድረሱን ይህም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚያደርጉት ድጋፍ በአገራቸው ጉዳይ ላይ ያላቸው ቁርጠኝነት ያረጋገጡበት ልዩ ክስተት መሆኑን አመልክተዋል።

"ዛሬን ሳይጨምር ከ25 ሚሊየን ብር በላይ ነው እዚህ ኤምባሲው ከተከፈተ ጀምሮ መሸጥ የቻልነው። ይሄ ለአገራችሁ ልማት እናንተም በውጭ ምን ያህል ዘብ እንደቆማችሁ የሚያሳይ ትልቅ ክስተት ነው።" ብለዋል።

የግድቡን የ6 ዓመታት የግንባታ ሂደትና ፋይዳ በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት በዶሃ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዳንኤል ወልደ ስላሴ በበኩላቸው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብም ድህነትን በመፀየፍ ዋነኛ ጠላታቸው እድርገው እጅ ለእጅ ተያይዘው እየገነቡት ያለ ታሪካዊ ፕሮጀክት ከመሆኑም በላይ የዜጎችን የቁጠባ ባህል እንዲዳብር ካለው ፋይዳ አንፃር በኳታር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የጎረቤት ሃገር ዜጎችና የኢትዮጵያ ወዳጆችም ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። 

በዝግጅቱ ላይ በቦንድ ሽያጭ ሳምንት የተሳተፉ ግለሰቦች፣ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ የልማት ማህበራት ፣የሚሲዮኑ ዲፕሎማቶችና ሎካል ሰራተኞች፣ የህዳሴው ምክር ቤቱ አባላትና ሌሎች ከልዩ ልዩ ኩባንያዎችና የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉ ሲሆን በዝግጅቱ ከ30 ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር ከቦንድ ሽያጭና የገቢ ማሰባሰቢያ ምንጮች መሰብሰብ ተችሏል። የህዳሴውን ግድብ ቦንድ ግለሰቦችና ተቋማት የቦንድ ሰርተፍኬታቸውን ከክቡር አምባሳደሩ እጅ ተቀብለዋል።

በተያያዘ ዜናም ሚሲዮኑ በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ስሙ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መጋቢት 2 ቀን 2ዐዐ9 በወገኖቻችን ላይ በደረሰው አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በድጋሚ የገለፀ ሲሆን  ህይወታቸውን ላጡ ዜጎቻችን ቤተሰቦችና መላው ህዝባችን መፅናናትን ተመኝቷል።

=====================================END============================================= 

"በቀጣዮቹ 3 ወራት የኢትዮጵያና ቀጠር ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ ስራዎች ይሰራሉ።" አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ለቀጠር ዕለታዊ የዓረብኛ ጋዜጣ የተናገሩት

December 24, 2016

በቀጠር የኢፌዲሪ ልዩ መለዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ሰሞኑን በቀጠር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራው የልዑካን ቡድን በአገራችን ያደረገውን ይፋዊ የስራ ጉብኝትና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከአል ረያን ቀጠር ዕለታዊ የአሪብኛ ጋዜጣ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ትርጉም እንደሚከተለው አቅርበናል። 

"በቀጣዮቹ 3 ወራት የኢትዮጵያና ቀጠር ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ ስራዎች ይሰራሉ።"

ቀጠር በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ያላት አዎንታዊ ሚና ማጠናከር ያስፈልጋል።

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ

  • ኢትዮጵያና ቀጠር በንግድና ኢንቨስትመንት በቱሪዝምና በመሰረተ ልማት ዘርፍ ለመስራት የሚያስችላቸው 11 የጋራ መግባቢያ ሰነዶችንና ስምምነቶችን ከዚህ ቀደም መፈራረማቸው፤

  • ቀጠር በኢትዮጵያ ካለው ሰፊና ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ መጠቀም እንዳለባት፤

ዝርዝር ጉዳዮች፤

  • በቀጠር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ያደረጉት ጕብኝት ውጤት ምን ይመስላል?

በክቡር የቀጠር የውጭ ጉዳይ ሚንስትር መሃመድ ቢን አብዱልራህማን ቢን ጃሲም አል ታኒ የተመራው የልኡካን ቡድን ሰሞኑን በኢትዮጵያ ያደረገው ጉብኝት በዋናነት ሁለቱ ሃገራት ለረዥም ጊዜ የዘለቀውን ታሪካዊ ግንኙነታቸውን በላቀ ደረጃ ለማሳደግ በማሰብ የተከናወነ ነው። በመሆኑም ሁለቱ ወገኖች ንግድና ኢንቨስትመንት፣ መሰረተ ልማት ግንባታ እና ቱሪዝም መስክ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ እንዲደርሱ አስችሏቸዋል።

የሁለቱ ሃገራት የግንኙነት ወሰናቸው እየሰፋና እየተጠናከረ ለመምጣቱ በዚህ ጉብኝት ወቅት ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን በእስካሁኑ የተፈረሙት 11 ያህል የመግባቢያ ሰነዶች እና ስምምነቶችም ለዚህ ግንኙነት መጠናከር ማሳያዎች ናቸው። በኢትዮጵያና በቀጠር መካከል የተደረሱት እነዚህ ሥምምነቶች ግንኙነቱን ሊያጠናክሩ በሚችሉበት አግባብ የተመሰረቱና የጋራ ጥቅምን በሚያስጠብቁ መልኩ ገቢራዊ እንደሚሆኑም ይጠበቃል።

ሰሞኑን በተደረገው ጉብኝት ወቅትም እነዚሁ የትብብር ስምምነቶችና የመግባቢያ ሰነዶች ባጭር ጊዜ ውስጥ ተጨባጭ ውጤት እንዲያመጡ በሚያስችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ለማድረግ ከማስቻሉም በላይ ሁለቱም ወገኖች የንግድና ኢንቨስትመንት ተሳፍአቸውን ማሳደግና የባህልና የህዝብ ለህዝብ እንዲሁም ፖለቲካዊ ግንኙነቶቻቸው ላይ ባተኮሩ ሀገራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይም በስፋት ለመምከር ችለዋል።

ኢትዮጵያ ለዓለም ሠላምና ደኅንነት በተለይ በምሥራቅ አፍሪካ ሠላምና መረጋጋት እንዲረጋጋጥ እያበረከተች ላለው አዎንታዊ አስተዋጽኦ በቀጠር መንግስት በኩል እውቅና የተቸረው ሲሆን ሃገሪቱ በሶማሊያ፣ በደቡብ ሱዳንና፣ ሌሎች አገራት የሠላምና ፀጥታ ጉዳይ ላይ ያላት ተሳትፎ በተመለከተ ሰፊ ውይይት ለማካሄድ የረዳ ነበር ጉብኝቱ። በተለይም በሶማሊያ የተመሰረተውን ሁሉን አቀፍ መንግስትና የተገኘውን ሠላምና መረጋጋት ለማስቀጠል ሁለቱ ሃገራት ድጋፍ በሚያደርጉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

በሌላም በኩል ኢትዮጵያ በመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አባል ሆና እንደመመረጧ በዚሁ በሚኖራት ቆይታ የሚኖራትን የሰላምና ደህንነት ማስከበር ሚና እንዲሁም ቀጠር በአፍሪካ ቀንድ ግጭቶች እንዲወገዱና ሰላም እንዲሰፍን የምታካሄደው የአስታራቂነት ሚና  ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሁለቱ ሃገራት በጋራ ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

  • በጉብኝቱ ወቅት በዋናነት ምክክር የተደረገባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ምን ምን ናቸው?

በአጠቃላይ በጉብኝቱ ወቅት የተዳሰሱ ዋና ዋና ጉዳዮች ከዚህ ቀደም በሁለቱ ሃገራት መካከል የተፈረሙ ስምምነቶች ወደ ተጨባጭ ትብብር ለማስፋት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች፣ በአፍሪካ ቀንድ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ በሚሰሩ የትብብር መስኮች በዚህ መስክ በአለማቀፍ መድረኮች ያላቸውን አውንታዊ ሚና ማጠናከር በሚቻልበት እንዲሁም የሁለቱን ሃገራት የንግድና ኢንቨስትመንት፣ የባህልና የህዝብ ለህዝብ ትስስራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚችሉባቸው ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን የዳሰሱ ናቸው።

  • ስለ ሁለቱ ሃገራት ግንኙነትና የወደፊቱ አንደምታ በማስመልከት ምን አስተያየት አለዎት?

የኢትዮጵያና ቀጠር የሁለትዮሽ ግነኙነታቸውን ለማጠናከር በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ። በኢትዮጵያና በቀጠር መካከል ጠንካራ ግንኙነት እንዳለ ማሳያ ከሆኑት መካከል ቀደም ሲል የሁለቱ አገራት መሪዎች ጉብኝት ማድረጋቸውንና  የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ማቋቋምን ጨምሮ በርካታ የኢኮኖሚና የቴክኒክ ትብብር ስምምነት መፈራረማቸው ይጠቀሳል። የሁለቱ አገራት የባህልና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያችሉ መድረኮችም እየተበራከቱ ይገኛሉ። የኳታር መንግስት በኢትዮጵያ ያሉ ሰፊና ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮችን እንዲጠቀምና የሁለቱም አገራት የንግድ ማኅበረሰቦች ያላቸው ግንኙነት ትርጉም ባለው ደረጃ እንዲቀየር የሚያስችል ስራም በስፋት ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል። በቀጣይም ይሄው በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስና ዘላቂነቱንም በማስጠበቅ የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ እንደሚቀጥል ተስፋ አለኝ።

  • ሁለቱ ሃገራት በቀጣይ ለማዘጋጀት ያሰቡት ፍኖተ ካርታ/Raodm  ap/ ይዘቱ ምንድነው?

ፍኖተ ካርታው በዋናነት አገራቱን የጋራ ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ የኢኮኖሚ ዘርፎችን የሚለይ ነው። አገራቱ በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በባህል፣በአከባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተባብረው የሚሰሩባቸውንም መስኮች የሚለይና ስምምነቶቹን ወደ ተጨባጭ ትብብር ለማስፋት የሚያግዝ ነው።

  • በኢትዮጵያ የኳታር ኢንቨስትመንት መጠን ምን ያህል ነው?

አሁን ያለው የቀጠር የኢንቨስትመንት ተሳትፎ በጅምር ላይ ያለ ነው። በዚህ ረገድ ያለው ትብብር በአገልግሎት ዘርፍ ማለትም  በአየር በረራ ዙሪያ ላይ ያተኮረ ነው ። የሁለቱ አገሮች አየር መንገዶች በሳምንት ሦስት ጊዜ ከዶሀ አዲስ አበባ የደርሶ መልስ በረራ ያደርጋሉ ። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ምርቶች ማለትም አበባ ፣ ፍራፍሬ እና የስጋ ምርቶች በቀጠር የገበያ እድል እያገኙ ነው። 

 

  • ኢትዮጵያ ለውጭ ኢንቨስተሮች የምትሰጣቸው ማበረታቻዎች ምን ምን ናቸው?

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር  ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ከሆኑ መዳረሻዎች በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች ። ሰፊ የኢንቨስትመን እድሎች አሏት ። በተለይም አዲስ አበባ የበርካታ ተቋማት ፣ የዲፕሎማቲክ ማህረሰብ መገኛ ፣ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን በቱሪዝም ማለትም በአገልግሎትና ሆቴል መስኮች ሰፊ የኢንቨስትመንት እድሎች አሏት  ።   

የውጭ ባለሃብቶችን የሚያበረታቱ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች፣ አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት፣ ሰፊ የሰው ሃይልና  የሃይል አቅርቦትና ሌሎችም ማበረታቻዎች ኢትዮጵያን በውጭ ባለሀብቶች ቀዳሚ የኢንቨስትመንት ተመራጭ እያደረጓት ነው። ከዚህ ጎን ለጎን እየተገነባ ያለው የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ሃገሪቱን ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በተለየ መልኩ ተመራጭ አድርጓታል። ባለሀብቶች የተመቻቸላቸው ከቀረጥ ነፃ የሆነ ገበያ እና ምርቶቻቸውን ወደ መካከለኛው ምስራቅ እስያ፣አሜሪካና አውሮፓ የሚልኩበት አሰራርም ኢንቨስተሮች ሀገሪቱን እንዲመርጧት እያደረገ ነው። መንግሥት የውጭ ባለሃብቶችን ለማበረታታት የግብር ዕፎይታ ፈቅዷል፡፡ ስለሆነም የቀጠር ኢንቨስተሮችም በነዚህ መስኮችና  በመሠረተ ልማት ግንባታ ማለትም በመሰረተ ልማት ፣ በመንገድ ፤በባቡር ፣ በሃይል አቅርቦት እንዲሁም በግብርና ኢንቨስት እንዲያደርጉ ይመከራል።

  • ኢትዮጵያ በክፍለ አህጉሩ ይምትጫወተው ሚና ምንድ ነው?

ኢትዮጵያ በፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ ያለችና በርካታ ሊለሙ የሚችሉ የኢቨስትመንት አማራጮች ያሏት ሃገር ናት። ሃገሪቱ ለልማት ካላት ምቹነት ባሻገር ሃገሪቱን ለማዘመን መንግስት በክፍለ አህጉሩ በአህጉሩና ከሌሎች ሃገራት እንዲሁም አህጉራዊና አለማቀፋዊ ተቋማት ጋር የሚሰራባቸው የትብብር መስኮችና እየሰፉና እየተጠናከሩ ይገኛሉ። ከሁሉም የልማት ሃይሎች ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ባተኮረ መልኩ ትንቀሳቀሳለች። ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሠላምን ለማምጣት የምታደርገው ጥረት በዓለም ኅብረተሰብ ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ ሆኗል። ኢትዮጵያ በተለይም የሶማሊያንና የደቡብ ሱዳንን ፀጥታ ለማረጋገጥ እያበረከተች ያለችው አስተዋጽኦ የሚደነቅ እንደሆነም የብዙዎች እምነት ነው።

በአጠቃላይ ሲታይ አገሪቱ የምትከተለው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ብቻም ሳይሆን ቀጠናውን በመሰረተ ልማት እንዲተሳሰር በሂደትም በአፍሪካ ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመጣ አበክራ እየሰራች ያለች አብነትም መሆን የቻለች ሃገር ናት። በዚህ በኩል አሁን በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ለጎረቤት ሀገሮችና ለተፋሰስ አገሮች የኤሌክትሪክ ሃይልን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማሰተላለፍ ትልቅ ሚና ይጫወታል። የህዳሴ ግድብ ግንባታ  የሀይል ፍላጎቷን ስለሚያሟላላትና ሌሎች በርካታ ጥቅሞች ስለሚያስገኝ ሱዳን ከምር ትደግፋዋለች። የህዳሴ ግድብ ግንባታ በተፋሰሱ ፣ በጎረቤት አገሮችና እንዲሁም በባህረ ሠላጤ አገሮች መካከል የኢኮኖሚ ትብብር እንዲጎለብት ከፍተኛ ሚና ሊጫወት ይችላል። ተመሳሳይ የአፍሪካ ቀንድ ሃገራትን ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሚያጠናክሩ ግዙፍ የባቡርና የመንገድ ፕሮጀክቶችንም ተግባራዊ እያደረገች ነው። ከእነዚህ መካከልም ኢትዮጵያን ከጅቡቲ ኬኒያና ሱዳን የሚያስተሳስሩ የኤሌክትሪክ ሃይል የመንገድና የባቡር መስመሮች ግንባታ ይጠቀሳሉ።

=======================================//=====================================

ኳታር የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአሸርቅ ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ አደረጉ።

November 08, 2016

ኳታር የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአሸርቅ ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ አደረጉ።
ክቡር አምባሳደር በኳታር እና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነት በተለይም የኳታር ባለሃብቶች መዋዕለ ነዋያቸውን በኢትዮጵያ አንዲያፈሱ መንግስታቸው እያደረገ ስላለው ልዩ ድጋፍ፣ በአፍሪካ ቀንድ አከባቢ ሰላምንና መረጋጋትን ለማስፈን የኢትዮጵያ ሚና ምን እንደሚመስል፣ እንዲሁም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባ በታችኛው ተፋሰስ ሀገሮች እና ለሌሎች የአከባቢው ሀገራት ያለው ፋይዳና አንዳንድ የግብፅ መገናኛ ብዙሃን እያቀረቡ ስላሉት የተዛቡ መረጃዎችን አስመልክቶ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
እኛም ጋዜጣው ያደረገላቸውን ቃለ መጠይቅ የሚያውጣውን ሙሉ ቃል ወደፊት ተከታትለን የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

"መንግስት በአሁኑ ወቅት ለሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ ከህዝቡ ጋር የጀመረውን ምክክር አጠናክሮ መቀጠል አለበት። በኛም በኩል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆኑ የበኩላችንን ሚና መወጣት ይኖርብናል።" በኳታር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን

November 03, 2016

"መንግስት በአሁኑ ወቅት ለሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ ከህዝቡ ጋር የጀመረውን ምክክር አጠናክሮ መቀጠል አለበት። በኛም በኩል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆኑ የበኩላችንን ሚና መወጣት ይኖርብናል።" በኳታር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን

"በአሁኑ ወቅት መንግስት ከምንጊዜውም በላቀ የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ቁርጠኛ ነው። ለዚህም ማሳያ የሚሆኑ በጥልቀት የመታደስ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል።" ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ

ነዋሪነታቸው በኳታር ዶሃና አከባቢዋ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጽያውያን ፣ ትውልደ ኢትዮጽያውያን የሃይማኖት አባቶችና የህዝባዊ ማህበራት ተወካዮች ካለፈው መስከረም ወር መግቢያ ላይ ከአካሄዱት ህዝባዊ ውይይት የቀጠለ ሁለተኛውን መድረክ  በኤምባሲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳዮች ላይ በተለይም በኣስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም ላይ አተኩረው ተወያይተዋል።

በውይይቱ መክፈቻ ላይ የሚሲዮኑ መሪ ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነት እና አዋጁ መውጣቱ ባስገኛቸው ጥቅሞች ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የውይይቱ ተሳታፊዎችም መንግስት ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮችና ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

በኳታር የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስጥጣን አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በውይይቱ መክፈቻ ላይ እንዳስታወሱት ሃገሪቱ በተለያዩ መስኮች ያስመዘገበቻቸው  ከሁለት አስርት አመታት በፊት የነበረውን ከድህነት ወለል በታች ይኖሩ የነበሩ የሃገሪቱን ዜጎች አሃዝ በግማሽ መቀነስና በዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባቱንና አህጉራዊና አለማቀፋዊ ተሰሚነትን በከፍተኛ ደረጃ ማሻሻል የቻለ ነው።

ይሁንና እድገቱን ተከትሎ የህዝቦች የላቀ የልማት ፍላጎት በእጅጉ ማደጉ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ማዳረስ ባለመቻሉ በሃገሪቱ አንዳንድ አከባቢዎች ተቃውሞ ማስነሳታቸውን የገለጹት ክቡር አምባሳደሩ እነዚሁ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችንና ቅሬታዎችን ተገን በማድረግ ሀገራዊ እድገቱ ያላስደሰታቸው የጥፋት ሀይሎች በውጭ ከሚገኙ የአሸባሪና ጸረ ሰላም ሃይሎች ጋር በመሆን የህዝቡን ጥያቄ ወዳልተፈለገ ሁኔታ በመምራት በሀገሪቱ አንዳንድ አከባቢዎች ሁከትና ብጥብጥ እንዲከሰት ብሎም እንዲባባስ ማድረጋቸውን አብራርተዋል።

በጊዜ ሂደት ይሄው አመጽና ግርግር በህዝቡና በአጠቃላይ በሃገሪቱ ላይ ከፍተኛ የሽብር ስሜት ውስጥ የከተተ፣  የሰው ህይወት መጥፋትና ከፍተኛ ንብረት ውድመት ያስከተለ በመሆኑም መንግስት በህገ መንግስቱ የተጣለበትን ግዴታ ለመወጣት ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማውጣት መገደዱንና በዚህም በአሁኑ ወቅት ሃገሪቱ ቀድሞ ወደምትታወቅበት ሰላማዊና የተረጋጋ ሁኔታ መመለስ መቻሉን ተናግረዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሙሉ ለሙሉ ተፈጻሚ ይሆን ዘንድ በውጭ የሚኖሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ እጅጉን አስፈላጊ እንደመሆኑም በዶሃና አከባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሽብር ተግባር ላይ የተሰማሩና ማናቸውንም አይነት በአዋጁ ክልከላ የተደረገባቸውን እንቅስቃሴዎች የሚያደርጉ አካላትን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መምከር እንዳለባቸው ለመድረኩ ተሳታፊዎች መክረዋል።

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት መንግስት ከምንጊዜውም በላቀ የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ቁርጠኛ መሆኑን በማስታወስ በዚህ ሂደት የመድረኩ ተሳታፊዎች አፍራሽ ተልእኮ ያላቸውንና የሃገሪቱን መጻኢ እድል ለማቀጨጭ የሚንቀሳቀሱ አካላትን በመታገል የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ መክረዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም እንዲሁ ዜጎች ሃገሪቱ ከድህነት ለመውጣት ያለፈችባቸውን ውጣ ውረዶችና የተገኙ ድሎች እንዲሁም ተግዳድሮቶችን በተመለከተ በበቂ ሁኔታ የሚረዳበት የመረጃ ስርዓት አለመዘርጋቱ፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የህዝብ ተጠያቂነት ያለበት አሰራር በበቂ ሁኔታ አለመዳበር፣ ለህዝብ ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥባቸው ሁኔታዎች አለመበራከታቸው እንዲሁም በሃገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የመንግስትን ስልጣን ለመያዝ አልያም ከመንግስት ጋር ለመስራት የሚፈልጉ ሃይሎች ያሉባቸውን ክፍተቶች መዝጋት አለመቻላቸው ህዝቡን ለጥፋት ሃይሎች ሰለባ መዳረጋቸውና ሃገሪቱንም ወደ አላስፈላጊ ቀውስ እንድትገባ አድርገዋት እንደነበር ተናግረዋል።

በተለይም ህዝቡ ለሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ማናቸውንም አይነት ጥያቄዎች መንግስት ምላሽ የሚሰጥባቸው ሁኔታዎች ፈጣን አለመሆናቸው በሃገሪቱ አንዳንድ አከባቢዎች ተከስቶ ለነበረው ሁከትና ብጥብጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከቱን በመግለፅ ከዚህ በኋላ ተመሳሳይ ሁኔታዎች እንዳይፈጠሩ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

በውጭ ሃገር የሚንቀሳቀሱ የአሸባሪ ቡድኖችም ሆኑ ጸረ ሰላም ሃይሎችን እንቅስቃሴ በዘላቂነት ለመግታት እንዲቻልም መንግስት የጥፋት ሃይሎቹ ከሚገኙባቸው ሃገራት ጋር ያለውን መልካም ዲፕሎማሲያዊና ስትራቴጂካዊ  ግንኙነት በመጠቀም በህግ የሚጠየቁበትን አግባብ መፍጠር አለበትም ሲሉ የመድረኩ ተሳታፊዎች አሳስበዋል።

በዚህ ረገድ በዶሃ ኳታር የሚገኝ ከፅንፈኛና አሸባሪ ድርጅቶች ጎን በመቆም የሃገራችንን ሰላምና ልማት ለማደናቀፍ የሚሰሩ ዲያስፖራ አባላት ላይ መንግስት የተጠናከረ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ አለበትም ብለዋል። በመንግስት በኩል ለነዚህ ጉዳዮች በቂ ምላሽ መስጠት እንዲችል በአፋጣኝ ከህዝቡ ጋር የጀመረውን ምክክር አጠናክሮ እንዲቀጥል በመጠየቅም ለዚህም ስኬት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት በማመን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ይቻል ዘንድ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ተናግረዋል።

በመጨሻም ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን በየትኛም ወቅት የሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ህዝባዊ መሰረት ያላቸው ሆነው እስከቀረቡ ድረስ መፍትሄዎቻቸውን ከማበጀት አንስቶ በሚፈለገው ደረጃ ምላሽ እንዲያገኙ የህዝቡ የነቃ ተሳትፎ ምትክ የሌለው መሆኑን በማስገንዘብ ይህንኑ ተሳትፎአቸውን አጠናክረው በመቀጠል ከመንግስት ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፈዋል።

              ===================================END====================================

ዘጠነኛው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሰንደቅ አላማ ቀን "ሰንደቅ ዓላማችን የሉአላዊነታችን መገለጫ ፣ በብዝሃነት ላይ ለተመሰረተው አንድነታችን አርማ ነው! " በሚል መሪ-ቃል በዶ ኳታር የኢፌዲሪ ኤምባሲ ተከበረ::

October 16, 2016

ዘጠነኛው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሰንደቅ አላማ ቀን "ሰንደቅ ዓላማችን የሉአላዊነታችን መገለጫ ፣ በብዝሃነት ላይ ለተመሰረተው አንድነታችን አርማ ነው! " በሚል መሪ-ቃል በዛሬው እለት ጥቅምት 7 ቀን ከጠዋቱ 4 ሰዓት (10 PM) በኤምባሲያችን ቅጥር ግቢ በቀጠር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ልዩ መልእክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ፣ ዲፕሎማቶች ፣ የኤምባሲው ሰራተኞች እንዲሁም በዶሃ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በደማቅ ስነስርአት ተከበረ::
በበአሉ ላይ ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ባስተላለፉት መልዕክት ሰንደቅ ዓላማችን የሉአላዊነታችንና የማንነታችን መገለጫ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሊጠብቀውና ሊንከባከበው ይገባል ብለዋል::
ክቡር አምባሳደር አክለውም የአንድነታችን መሰረት የሆነው ሰንደቅ አላማችን ሁሉንም የሃገራችን ብሔር ብሔረሰቦችን በአንድ ጥላ ስር ያሰባሰበ በመሆኑ ይህን አንድነታችንን ለመሸርሸር የሚለፉ የጠባብና የትምክተኛ ኃይሎችን በንቃት መታገልና በሰንደቅ አላማችን ያገኘነውን አንድነታችንን ለማስቀጠል በዶሃ የሚኖሩ ዲያስፖራ አባላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል::
በመሆኑም በበአሉ ላይ የተገኙ የዲያስፖራ አባላትም የአንድነታችንና የሉአላዊነታችን መገለጫ የሆነውን ሰንደቅ አላማችንን በጋራ ሆነው ለመንከባከብና ለመጠበቅ ቃል ገብተዋል::

ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኳታሩ አል ፋይሰል ሆልዲንግስ ኩባንያ ባለቤትና ሊቀ መንበር ጋር ተወያዩ።

November 15, 2016

በኳታር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኳታር በግዙፍነታቸው ከሚታወቁት አንዱ ከሆነውና አል ፋይሰል ሆልዲንግስ ከተሰኘው ኩባንያ ባለቤትና ሊቀመንበር ከሆኑት ሼክ ፋይሰል ቢን ቃሲም አል ታኒ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ በዚሁ ወቅት እንደገለጹላቸው ኢትዮጵያ ቅድሚያ የምትሰጣቸውን እንደ ጨርቃጨርቅ ፣ ቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ የቱሪዝምና ግብርና እንዲሁም በኮንስትራክሽን ዘርፍ ከፍተኛ አቅምና እድል በመኖሩ በመስኩ ቢሰማሩ ውጤታማ ይሆናሉ። በሁሉም የማምረቻ ኢንዱስትሪ መሰኮች ላይ የሚሰማሩ ከሆነም እንዲሁ፤ መንግስት ከሌሎቹ ዘርፎች በተለየ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው አረጋገጠውላቸዋል።

ኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት ያስመዘገበችው ምጣኔ ሃብታዊ እድገት የፈጠራቸው መልካም አጋጣሚዎችን በመጠቀምም ሆነ የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትር ዘርፎች ላይ ቢሰማሩ በላቀ ሊጠቀሙ እንደሚችሉ የተናገሩት ክቡር አምባሳደሩ በዚህ ሂደት መንግስት የሚሰጣቸው ልዩ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችንም ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉም አረጋግጠውላቸዋል።

ክቡር አምባሳደሩ የኢትዮ-ኳታር ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ገልጸው ይህንን መሰረት በማድረግ የኳታር ኢንቨስትመንት እየሰፋ መምጣቱንና ኩባንያቸውም በሃገሪቱ የውጭ ኢንቨስትመንት ላይ እንደሚሰማራ ጽኑ እምነት እንዳላቸውንም ጠቅሰዋል።

የአል ፋይሰል ሆልዲንግስ ኩባንያ ባለቤትና የቦርድ ሊቀመንበር ሼክ ፋይሰል ቢን ቃሲም አል ታኒ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታና አማራጮች እስመልክቶ ስለተሰጣቸው ማብራሪያ አመስግነው ኩባንያቸው ወደፊት በሃገራችን በተለይ በሆቴልና ቱሪዝም፣ የመኖሪያ ቤቶች (ሪል ስቴት)፣ በትምህርት፣ በግብርናና የማምረቻው ኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ የሚሰማራበትን እድል እንደሚያይ ገልጸዋል። ለዚህም በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ በተጨባጭ ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ማበረታቻዎችን ለይቶ ማወቅ እንዲቻል የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

አል ፋይሰል ሆልዲንግስ ኩባንያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1960ዎቹ አካባቢ የተቋቋመና በኳታር ግንባር ቀደም ከሚባሉ የግል ኢንቨስትመንቶች አንዱ ሲሆን በዋናነትም በኮንስትራክሽን በንግድ ትራንስፖርት ትምህርትና መዝናኛ በአገልግሎት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እንዲሁም በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ እየሰራ የሚገኝ ነው።

የሃገሪቱን ህዳሴና ህብረብሄራዊ እሴቶችን የሚሸረሽሩ አፍራሽ ሃይሎችን በመዋጋት ሂደት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሚናቸውን እንዲያጠናክሩ በኳታር የኢፌዲሪ ኤምባሲ ጥሪ አቀረበ። ዝክረ መለስ 4ተኛ የሙት ዓመት መታሰቢያ፣ የትግራይ ልማት ማህበር በዶሃ ኳታር የተመሰረተበት ሁለተኛ ዓመትና የአሸንዳ በዓል በዶሃ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

September 03, 2016

ዝክረ መለስ 4ተኛ የሙት ዓመት መታሰቢያ፣ የትግራይ ልማት ማህበር በዶሃ ኳታር የተመሰረተበት ሁለተኛ ዓመትና የአሸንዳ በዓል በዶሃ የሱዳን ኮሚኒቲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል::

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት በኳታር የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሰጡት በሳል አመራር የትግራይ ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ጋር በመሆን በሀገራቸው በሰላም በመኖር በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ በመሳተፍ የሀገሪቱ የድህነት ታሪክ እንዲቀየር ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አስታውሰዋል።

በሀገሪቱ የሚካሄደውን ልማትና እያስመዘገበች ያለውን እድገት እንዲሁም በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተውን ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማስቀጠል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስና ሌሎች ሰማዕታትን ራዕይ  ሙሉ በሙሉ እውን ለማድረግ በውጭ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ሚና ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው መክረዋል።

የውጭ ሃይሎች በተለይ የማህበራዊ ሚዲያው እንደ ዋነኛ ማደናገሪያ ስልት በመጠቀም ተከታታይ ብሄር ተኮር አና የጥላቻ ውዥንብር በመንዛት ስልጣን በአቋራጭ የመያዝ ዓላማቸውን ለማስፈፀም አልመው  እየሰሩ መሆናቸውንም ያብራሩት እምባሳደር ምስጋኑ በተለይም በአሁኑ ወቅት እየተመዘገበ ያለውን ፈጣንና ተከታታይነት ያለው ልማትና እድገት ያላስደሰታቸው በውጭ ሃገራት የሚኖሩ የአሸባሪ ቡድኖች ተላላኪዎች የሚፈጽሙት እፍራሽ ተልዕኮ በጽኑ እንዲታገሉት አሳስበዋል።

 "ብሄር ብሄረሰቦች አብረን ስንኖር የማይዋጥላቸው በርካታ ጠላቶች እንዳሉን አውቃችሁ ኢትዮጵያዊነታችሁን በማጉላት በየአከባቢያችሁ በተለይ ይሄ የአብሮነት ጉዞአችንን የሚያጠናክሩ ስራዎችን መስራት ይኖርብናል።" ብለዋል። 

በአሁኑ ወቅትም መንግስት በሃገር ቤት ሁከትንና ብጥብጥን የሚመሩና እንዲባባስ የሚያደርጉ አካላትንም ከሰላማዊው ሕዝብ በመነጠል የማጥራት ሥራ መጀመሩን አስታውቀዋል። መንግስት በየደረጃው የተለያዩ መድረኮችን በማመቻቸት ከህዝቡም ይሁን ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚቀርቡ የልማት እና የዴሞክራሲ ጥያቄዎችን ለመፍታት ጥረት እያደረገ ነው ያሉት አምባሳደሩ ሕብረተሰቡ ለሚያነሳቸው ማናቸውም አይነት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ፈጣንና ዘላቂነት ያለው መፍትሄ ለመስጠት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛና ሙሉ ቁመና ላይ ይገኛልም ብለዋል።

"ከምንግጊዜም በላይ በነዚህ ጉዳዮች ህዝባችን የሚያነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢና ህዝባዊ በመሆናቸው መንግስታችን በየትኛውም መልኩ የህዝቡን ጥያቄ ለመፍታት የሚችልበት ሙሉ ቁመና ላይ ነው ያለው።" ሲሉም አመልክተዋል።

የዝክረ መለስ 4ተኛ የሙት ዓመት መታሰቢያ፣ የትግራይ ልማት ማህበር በዶሃ ኳታር የተመሰረተበት ሁለተኛ ዓመትና የአሸንዳ በዓል አዘጋጆች በበኩላቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ራዕይን በማንገብ ሃገሪቱ የተያያዘችውን የህዳሴ ጎዞ የማስቀጠል ሚናቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል የገቡ ሲሆን በዕለቱ በዶሃና አከባቢው የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆችን ባቀፈው የልማት ማህበር ማጠናከሪያ ልዩ ልዩ ዝግጅቶችና የአሸንዳን በዓል የማክበር ስራዎችን አከናውነዋል::

     

ግንቦት 25 ቀን 2008 ዓ/ም

 

ግንቦት-20 አስከፊው ፋሽስታዊ የደርግ ስርዓት ውድቀት የተበሰረበት ብቻ ሳይሆን ለዘመናት በድህነትና ኃላቀርነት ስትማቅቅ ለነበረችው አገራችን ህዳሴዋን ጭምር ያበሰረ ልዩ ክስተት ነው:: ከድል ማግስት አንስቶ የተያያዝነው የእድገት ጎዳና ቀጣይነቱን በማረጋገጣችን ሃገራችን በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ ሃገራት ተርታ መሰለፍ ችላለች::''
በቀጠር የኢፈዲሪ ልዩ መልእክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች በሚከበረውና ዛሬ ማምሻው በሸራተን ዶሃ የቀጠር መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮችና ሌሎች የአለማቀፉ ዲፕሎማቲክ ኮሚኒቲ አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ዝግጅት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ ነው::
የበዓል ዝግጅቱ ነገም ሁሉንም ባሳተፈ መልኩ በዶሃ ስታዲየም በተለያዩ የሙዚቃና ሌሎች ዝግጅቶች የሚቀጥል ይሆናል::

ኢትዮጵያና ቃጣር ግንኙነት

May 08, 2016

 

በኢፌዲሪ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፊስካል ፖሊሲ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ሶፊያን አህመድ የተመራው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ትናንት በኳታር ይፋዊ የስራ ጉብኝት አካሄደ።
ጉብኝቱ የኳታር የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሀማድ ቢን ጃበር አልታኒ በቅርቡ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ የተካሄደ ነው፡፡
=======================================
በኢፌዲሪ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፊስካል ፖሊሲ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ሶፊያን አህመድ የተመራው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በኳታር ባካሄደው የስራ ጉብኝት ከዚህ ቀደም ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ በሃገሪቱ ባሉ የኢንቨስትመን አማራጮች ላይ ከተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ጋር ውይይት ካደረገውና 13 አባላትን የያዘው የኳታር ባለሃብቶች የልኡካን ቡድን በስፋት የመከረ ሲሆን ውይይቱም የኳታር ባለሃብቶች በግብርና፣ ሆቴልና ቱሪዝም፣ በሃይል አቅርቦትና የባቡር ትራንስፖርት እንዲሁም በጤናው ዘርፍ በኢትዮጵያ ለመሰማራት በሚያስችላቸው ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ እንዲኖረው ያስቻለ ነበር። 
ውይይቱን የተከታተሉት በቀጠር የኢፌዲሪ ኤምባሲ ተ/ጉዳይ ፈጻሚ አቶ ሽብሩ ማሞ እንደገለፁት፤የልኡካን ቡድኑ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነች አገር መሆኗና የኳታር ባለሃብቶች በተለያዩ ዘርፎች ቢሰማሩ ውጤታማ ሊሆኑ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ በጥናት የተደገፉ ሰነድ ማቅረብ የቻለ ሲሆን ውይይቱ በቀጣይ ለሚከናወኑ ተጨባጭ የትብብር መስኮች መደላደልን የመፍጠር አላማ ያለው ነው።
በኢትዮጵያ የመብራት ኃይል አቅርቦት፤ የባቡርና ሌሎች የመሰረተ ልማት ስራዎችና ሰፋፊ እርሻዎች እንዲሁም በሌሎች ትልልቅ ፕሮጀክቶች አካባቢ የኳታር ባለሃብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉ በኢትዮጵያ በኩል ጥሪ መቅረቡን ያስታወሱት አቶ ሽብሩ፤ ይህንኑ ተከትሎ ባለሃብቶቹ የኢንቨስትመንት ተሳትፎአቸውን ሊያረጋግጡ የሚችሉባቸው መድረኮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በቀረበው ጥያቄ መሰረትም በሁለቱም ወገኖች በኩል በተቋቋሙ የቴክኒክ ኮሚቴዎች አማካኝነት በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረገው ውይይት እየተጠናከረ መሄዱን አስታውቀዋል። ትናንት በተካሄደው የውይይት መድረክም ሁለቱም ወገኖች የኢንቨስትመንት ትስስሩን ውጤታማ ለማድረግ በይበልጥ ለመስራት መስማማታቸውን ገልፀዋል።
በተጨማሪም የልኡካን ቡድኑ ከቀድሞ የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሀማድ ቢን ጃበር አልታኒ ጋር ባደረገው ውይይትም የኳታር ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች ለማሰማራት በሚያስችሉና በቀጣይ መከናወን በሚገባቸው አብይ ጉዳዮች ላይ በስፋት መምከር መቻሉን ተናግረዋል።

የታላቁ የኢትዮጽያ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 5ኛ ዓመት በዓል

April 14, 2016

የታላቁ የኢትዮጽያ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 5ኛ ዓመት በዓል “ግድባችን የማንነታችን አሻራ ያረፈበት የህዳሴያችን ብርሀን ነው።“ በሚል መሪ ቃል በዶሀ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ከ150 በላይ ኢትዮጽያውያን ፣ ትውልደ ኢትዮጽያውያንና የጎረቤት ሀገር እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።  
በእለቱ ከ54,000(ሀምሳ አራትት ሺህ) የአሜሪካን ዶላር በላይ ቦንድ ሲሸጥ ከ110 በላይ ሰዎች ቦንድ ገዝተዋል::  
በዶሀ የህዳሴውን ምክር ቤት ከ1ዓመት በላይ በአመራርነት ላገለገሉ እንዲሁም  በቦንድ ግዥና ድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላት እውቅና ተሰጥቷቸዋል። የልማት ማህበራት፣ የሴቶችና ኮሚኒቲ ማህበራት በማህበራችው ውስጥ አባላትን በማሳተፍ እንዲሁም ሳንቲም አጠራቅመው፣ እቁብ ጥለው በቦንድ ግዚው ላይ ለተሰማሩ ዜጎች የእውቅና ሰርተፊኬት ከከፍተኛ ምስጋና  ጋር ተበርክቶላቸዋል ።የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራሙ ቀጥሎም ለሱዳን ኮሚኒቲ ማህበር እንዲሁም በግል ከፍተኛ የቦንድ ግዥ ለፈጸሙ ሱዳናዊያን ሰርተፊኬት በከቡር አምባሳደር ተበርክቶላቸዋል አምባሳደሩ በሰርተፊኬት አሰጣጡ ወቅት ሱዳን ወንድሞቻችን ላሳዩት አጋርነት ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል ።
ለበዓሉ ድምቀት የሆኑ ሌሎች የተለያዩ ዝግጅቶችም የተካሄዱ ሲሆን የኢትዮጽያ ኮሚኒቲ ማህበር የባህል ቡድን የተለያዩ ጭውውቶችን ፣ ሙዚቃና ባህላዊ ውዝዋዜዎችን በማቅረብ ታዳሚውን ሲያዝናና አምሽቷል።
በዚህ አስደናቂ ህዝባዊ ርብርብ በተደረገበት ዝግጅት መጨረሻም  ታዳሚዎቹ  “እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን”  በሚል መፈክር አስተዋፅኦቸው የግድቡን ግንባታ ከዳር እስከማድረስ  እንደሚቀጥል ገልፀዋል

የኳታር ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ጥሪ አቀረቡ

April 13, 2016

የኳታር ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ጥሪ አቀረቡ
የኳታር ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 6 ፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) የኳታር ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሰማሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀድሞው የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሃማድ ቢን ጃሲን የተመራውን የልዑካን ቡድን በፅህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በዚህ ወቅት "ኢትዮጵያ በበርካታ ዘርፎች የሚሰማሩ የኳታር ባለሃብቶችን ትፈልጋለች፤ ለዚህ የሚሆን አማራጭም አለ" ብለዋል።
ውይይቱን የተከታተሉት በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ፥ ሁለቱ አገራት በኢንቨስትመንት ያላቸውን ግንኙነት ለማሳደግ መስማማታቸውነ አንሰተዋል።
የቀላል ባቡር ፕሮጀክቶች፣ የታዳሽ ኃይልና የስኳር ልማት ባለሃብቶቹ ሊሰማሩባቸው የሚችሉ ዘርፎች መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
ሁለቱ አገራት ቀጠናው የተረጋጋና ለንግድና ኢንቨስትመንት አመቺ እንዲሆን በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።
የኳታር የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሃማድ ቢን ጃሲን በበኩላቸው፥ የአገራቸው የግል ዘርፍ ተቋማት በኢትዮጵያ ባሉት የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሳተፍ ፍላጎት አላቸው ብለዋል።
በዚህ ረገድ የሁለቱ አገራት የግሉ ዘርፍ ተቀራርቦ መስራት የኢንቨስትመንት መስተጋብሩን በእጅጉ እንደሚያሳድገው ነው የገለፁት።
የሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2008 አጋማሽ ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም ከሶስት ዓመት በፊት ግንኙነቱን መሻሻሉ ይታወሳል::

በዶሃና አከባቢው የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን!

March 01, 2016

 

 

ከትናንት በስቲያ የሚሲዮናችን የዜጎች ጉዳይ ክፍል የቀጠር መንግስት አዲሱን የሰራተኛና አሰሪ አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ በሙሉ ሃይሉ በመቀሳቀስ ላይ መሆኑንና ይህንኑ ተከትሎ በርካታ ቁጥር ያላቸውን የሃገራችን ዜጎች በቀጠር የስራ ስምሪት ህግን አላከበሩም በሚል መታሰራቸውን ተከትሎ በቀጠር የተመላሽ የውጭ ሃገር ዜጎች ማቆያ ማዕከል/Deportation Center/በመገኘት ዜጎቻችንን ያሉበትን ሁኔታ ለመጎብኘትና በጉዳዩ ላይ የመንግስታቸውን አቋም እንዲያስረዱ የማዕከሉን ምክትል ዳይሬክተር ሌትናንት ኮሎኔል አብዱልራህማን ፋክሪን ማነጋገሩንና ቀጣይ ውይይት እንደሚደረግ ማስታወቃችን ይታወሳል።

 

በትናንትናው ዕለት የሚሲዮናችን ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በተከታታይ ሦስት ቀን በቀጠር የተመላሽ የውጭ ሃገር ዜጎች ማቆያ ማዕከል/Deportation Center/ በመገኘት በዚያው ባሉ ከሁለት መቶ በላይ ዜጎቻችን ማነጋገር የቻሉ ሲሆን ከማዕከሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋርም ዜጎቻችን አስፈላጊውን የህግ ድጋፍ አግኝተው ጉዳያቸው በፍጥነት የሚታይበት መንገድ እንዲመቻች ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

 

ሚሲዮኑ በጉብኝቱ ወቅት በሁለት ቀን ውስጥ 150 ዜጎቻችን ከቤታቸው እና ከመንገድ ታፍሰው የተወሰዱ ሲሆን አብዛኛው የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ቢሆንም በመጡበት ካምፓኒ የማይሰሩ መሆኑን በተደረገው ጉብኝት ለመረዳት ተችሏል። በሌላ በኩል እስከአሁን ባለው አሰራር አንድ ሰራተኛ ከካምፓኒው ውጭ ለሁለተኛ አካል ተቀጥሮ ለማገልገል ከስፖንሰሩ የሥራ ፍቃድ መያዝ የሚገባው ሲሆን ከጥቂት ዜጎቻንን ውጭ ይህንን ስምምነት የያዙ አለመኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል። ጥቂት ዜጎቻችን የስፖንሰር ቅያሪ ላይ እያሉ የተያዙ ሲሆን ከመጡ ወር ያልበለጣቸውም በአፈሳው መያዛቸውን በተደረገው ጉብኝት ለመረዳት ተችሏል።

 

በተለያዩ ምክንያት ታስረው የቆዩ 54 ዜጎች በጉብኝት ወቅት መለየት የተቻለ ሲሆን ወደ አገር ቤት ለመግባት የፍርድ መጓተት ይታይብናል ያሉ ስምንት፣ ወደ ሃገራችን ከመግባታችን በፊት በአንድ ኩባንያ ውስጥ የሰራንበትን ገንዘብ ሊከፈለን ይገባል ያሉ ሃያ፣ የአሰሪ ለውጥ ሂደት ላይ/Sponsor Change/ በመሆናችን ጉዳያችን ተነጥሎ ሊታይልን ይገባል ያሉ አምስት ያህልና የተከሰስንበት ሁኔታ ህገ-ወጥ መሆኑን እናምናለን፤ ሆኖም ጉዳያችን በፍጥነት ታይቶ ወደ ሃገር ቤት እንድንሸኝ ይደረግ ያሉ የሚገኙ ሲሆን በጠቅላላ የ204 ዜጎቻችንን ጥያቄ በመያዝ ከቀጠር የተመላሽ የውጭ ሃገር ዜጎች ማቆያ ማዕከል ምክትል ዳይሬክተር ሌትናንት ኮሎኔል አብዱራህማን ፋክሪና ሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው ጋር ሰፊ ውይይት ያደረገ ሲሆን ለነዚሁ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥም ጥያቄ ቀርቧል።

 

በውይይቱ ወቅት እንደተገለጸውም የስፖንሰር ቅያሪ ያላቸው ዜጎቻችን ጉዳይ እየታየ መሆኑን፣ ያልተከፈላቸውን ገንዘብ ኩባንያው በአስቸኳይ እንዲከፍል እንደሚደረግ እና የቀረቡ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ማዕከሉ ብቻውን የሚያከናውነው ስራ ባለመሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ምላሽ የሚሰጥበት መሆኑን ምክትል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

 

ሚሲዮናችን በማዕከሉ በመገኘት ከሃላፊዎች እና ከዜጎቻችን ጋር ከሚያደርገው ምክክር ጎን ለጎን በማዕከሉ ታስረው በሚገኙም ሆነ በህገ -ወጥ የስራ ስምሪት ላይ ተሰማርትው በሚገኙ ዜጎቻችን አያያዝ ላይ የቀጠር መንግስት የሚቻለውን ያህል ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርግ ጫና ለማሳደር በርካታ ስራዎች በመስራት ላይ ሲሆን በቀጣይ ሳምንት ከቀጠር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የመንግስት ተጠሪዎች ጋር ውይይት ለማድረግ የሚያስችል ዝግጅት በመደረግ ላይ ነው።

 

ከቀጠር መንግስት የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው እ.ኤ.አ አቆጣጠር በ2015 ብቻ 5440 ኩባንያዎችና 3460 ሰውን ማስመጣት ፈቃድ የተሰጣቸው ግለሰቦች የሃገሪቱን የስራ ስምሪት ህግ ቁጥር 4/2009 ተላልፈዋል  በሚል በጥቁር መዝገብ ውስጥ ሰፍረዋል። በሰራተኞቻቸው ቅሬታ ቀርቦባቸውና በፍርድ ቤት ከተረጋገጠባቸው በኋላ እገዳ የተጣለባቸው እነዚሁ አካላት ከዚህ በኋላ ምንም አይነት አዲስ የሰራተኛ ቅጥር እንዳይፈፅሙ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

 

የህገ-ወጥ የቪዛ ንግድን በተመለከተም በሃገሪቱ ያለው ቁጥጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰ ያለው ችግር ሰፊ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ። እ.ኤ.አ በ2013 በዚህ ወንጀል ተከሰው የነበሩ አካላት 184 ኩባንያዎችና 1,203 ግለሰቦች ነበሩ። እነዚሁ የህገ ወጥ ቪዛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎችና ግለሰቦች እንዲሁም ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ ዜጎች የቀጠር መንግስት ወደ ሌላ ኩባንያ እንዲዛወሩና ስራ ላይ እንዲሰማሩ እያደረገ መሆኑን የሚገልፅ ቢሆንም ይህንን እድል አሟጦ ለመጠቀም እንዲቻል ወደ ቀጠር የመጡ ዜጎቻችን ማንነት በኤምባሲያችን የማይታወቁና የመጡ ዜጎቻችን በኤምባሲያችን ቀርበው ያልተመዘገቡና ሪፖርት ያላደረጉ በመሆኑ ተገቢውን ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ አዳጋች አድርጎታል።

 

በመሆኑንም ኤምባሲያችን እነዚህ ጉዳዮች ከመከሰታቸው በፊት ዜጎቻችን እንዲመዘገቡ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ጥሪ ያደረገ ቢሆንም እስካሁም ምንም ምላሽ ማግኘት አልተቻለም። ስለሆነም በሚያጋጥማችሁ ማንኛውም ጉዳይ ለኤምባሲያችን እንድታሳውቁ እየጠየቅን፣ ጉዳዩ እስከሚስተካከል ድረስ ተገቢውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ እንገልፃለን።

 

 

 

 

1 / 1

Please reload

 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

 News