የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 

ኤምባሲ

 ኳታር - ዶሃ

ርዕሰ ዜና

ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ  ጠቅላይ ሚኒስትር 

ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ 

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዲዳንት

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ከማርች 19-20/2019 በዶሃ ቀጠር የሁለት ቀናት ስኬታማ ጉብኝት አድርገዋል። የቀጠር የትራንስፖርትና ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር ጃሲም አህመድ አል ሱሌይቲ፣ በቀጠር የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሳሚያ ዘካርያ እና የኤምባሲው ዲፕሎማቶች በሃማድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

 

H.E. Sahle-Work Zewde

President of Federal Democratic Republic of Ethiopia

H.E Dr.Abiy Ahmed

The Prime minister of Ethiopia

 ክቡር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ 

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

 ክብርት ወ/ሮ ሳሚያ ዘከርያ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በዶሃ ልዩ መልክተኛ እና

ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር

መጋቢት 12/ 2011 ዓ/ም

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቀጠር ስኬታማ ጉብኝት አድርገዋል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ከማርች 19-20/2019 በዶሃ ቀጠር የሁለት ቀናት ስኬታማ ጉብኝት አድርገዋል። የቀጠር የትራንስፖርትና ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር ጃሲም አህመድ አል ሱሌይቲ፣ በቀጠር የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሳሚያ ዘካርያ እና የኤምባሲው ዲፕሎማቶች በሃማድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በጉብኝታቸውም ወቅት ከቀጠር አሚር ሼክ ተሚም ቢን ሃማድ አልታኒ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። በውይይቱም ሁለቱ አገራት በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚያደርጉትን ትብብር የበለጠ አጠናክረው በሚቀጥሉበት ሁኔታ፣ በዜጎቻችን ደህንነት፣ እንዲሁም በወቅታዊ የቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ደርሰዋል። የቀጠር ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ዘርፎች መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ በሚችሉበት ሁኔታ ላይም ተወያይተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከቀጠር ጠቅላይ ሚኒስትርና የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አብደላህ ቢን ናስር ቢን ኸሊፋ አልታኒ፣ እንዲሁም ከቀጠር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሃመድ ቢን አብዱልራህማን አልታኒ ጋር በቀጠር የሚኖሩ ዜጎቻችን ደህንነት እና በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጠር ከሚኖሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል። የማህበረሰቡ ተወካዮችም በቀጠር የሚኖሩ የዜጎቻችን መብትና ጥቅም፣ በልዩ ልዩ አገልግሎቶች፣ በወቅታዊ የአገራዊ ሁኔታ፣ እንዲሁም በቀጠርና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለተነሱት ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በዶሃ ቆይታቸውም የቀጠር የስፖርት ማዕከል የሆነውን የአስፓየር ዞን ፋውንዴሽን እና የእስላሚክ የጥበብ ሙዚየምን ጎብኝተዋል።

በመጨረሻም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቀጠር ለዓመታት ያክል በሆስፒታል ተኝታ ህክምና እየተከታተለች የምትገኘውን ወ/ሮ ሜሮንን እና ሌሎች ሁለት ዜጎቻችንን በሃማድ ሆስፒታል በአካል ተገኝተው ጠይቀዋል።
 

የካቲት 19 / 2011 ዓ/ም

ክብርት አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለቀጠር አሚር አቀረቡ።

በቀጠር የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ክብርት አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለቀጠር አሚር ሼክ ተሚም ቢን ሃማድ አልታኒ አቅርበዋል። በስነ-ስርዓቱም ግርማዊነታቸው ሼክ ተሚም ክብርት አምባሳደር ሳሚያን እንኳን ደህና መጡ በማለት፣ በቀጠር ቆይታቸው ተልዕኳቸውን በስኬት እንዲወጡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉላቸው ተናግረዋል።

ክብርት አምባሳደር ሳሚያ በበኩላቸው የቀጠር መንግስት ላደረገላቸው ደማቅ አቀባበል በማመስገን፣ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ለአሚሩ የላኩትን የሰላምታና የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል። ከዚህ በተጨማሪም በጠንካራ መሰረት ላይ የሚገኘውን የኢትዮጵያና የቀጠር የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር በትጋት እንደሚሰሩም አረጋግጠውላቸዋል።

ታህሳስ 4/ 2011 ዓ/ም

በቀጠር ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የኮሚኒቲ ትምህርት ቤት ለማቋቋም ህንፃና ፈቃድ ተሰጠ


በቀጠር አሚር ሼክ ተሚም ቢን ሃማድ አልታኒ መልካም ፈቃድ በዶሃ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መማሪያ የሚሆን የኮሚኒቲ ትምህርት ቤት እንዲከፈት የቀጠር መንግስት ቃል መግባቱ የሚታወስ ነው።
በመሆኑም ኤምባሲያችንና በቀጠር የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ከቀጠር ትምህርትና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር መንግስት የገባውን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ የክትትል ስራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል። 
በዚህ መሰረት Al Shahaniya ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ ሕንጻን ለትምህርት ቤቱ ግልጋሎት እንዲውል የቀጠር ትምህርትና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባቀረበው ሃሳብ መሰረት፣ የኤምባሲያችንና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር አመራሮች ሕንጻውን በአካል ተገኝተው ጎብኝተዋል። 
በጉብኝቱ ወቅት ሕንጻው እድሳት እንደሚያስፈልገው ታምኖበት የቀጠር መንግስት ወጪውን እንዲሸፍን ጥያቄ ቀርቦ ነበር።
በመሆኑም በቀጠር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉ ስልጣንና ልዩ መልዕክተኛ ክቡር አምባሳደር መታሰቢያ ታደሰ ኖቬምበር 28/2018 ከቀጠር ትምህርትና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝተው ውይይት ባደረጉበት ወቅት የቀጠር መንግስት የተጠቀሰው ሕንጻ በቀጠር ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የኮሚኒቲ ትምህርት ቤት ሆኖ እንዲያገለግል መፍቀዱን እና የእድሳት ስራውም በቀጠር መንግስት የሚሸፈን ሆኖ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጀመር በማሳወቅ፤ ይህንኑ ፈቃድ የሚገልጽ የፅሁፍ ማረጋገጫ ደብዳቤ ለኤምባሲው ተሰጥቷል። 
የትምህርት ቤቱ መከፈት በቀጠር እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት አንዱ ማሳያ እንደመሆኑ፣ የመማር ማስተማር ሥራው ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲቀጥል በርካታ ቀሪ ሥራዎች ያሉ በመሆኑ፣ ማህበረሰቡ፣ የኮሚኒቲው አመራርና ኤምባሲው ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል፡፡

1/17

Please reload

የዜና መፅሔት ቁጥር 2

ታህሳስ 24 2011 ዓ/ም

* Ethiopia Grants Visa on Arrival for Citizens of AU States.

* Ethiopia Sets the Standard With Election of First Female President and a Gender-Balanced Cabinet.

* Ethiopia, Eritrea, Somalia Agree To Frame Tripartite Relations.

 *The Council of EU describes Ethiopia’s reforms as a positive example for the Region.

* PM Dr. Abiy among 100 Most Influential Africans of 2018

* Leaders of Ethiopia, Sudan, and Djibouti Inaugurate Jimma Industrial Park

1/2

Please reload

 
 
Ethiopian_Airlines_Logo.svg.png
etv.png
ETO-Logo-1024x684.png

 News